የህዝባችን የመልማት ፍላጎት ጥያቄ ለመፍታት በት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህዝባችን የመልማት ፍላጎት ጥያቄ ለመፍታት በትኩረት እየሰራን ነው፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመራጩ ህዝብ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፡- በየጊዜው የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን አንዴ መመለስ ባይቻልም ደረጃ በደረጀ ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል፡፡

በተለይም በእቅዳችን ያልተካተቱና ህዝብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ካሉ እቅዳችን በመከለስ በዚህ ዓመት ትኩረት የሚሻቸውን በመለየት እና በእቅዳችን በማካተት በትኩረት እንሚሰሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ዘርፎች ለውጦች መመዝገባቸውን የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቴክኖሎጂ የተደረፈ በአንድ መሶብ አገልግሎቶችን በመስጠት ብልሹ አስራርንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ከህዝብ ጋር ተቀራርበን በሰራነው ስራ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍና ሀገራዊ ሁነቶችን ያለምን የጸጥታ ችግር ተከብረው እንዲውሉ መደረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ እቅድ የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል ተጨማሪ የውሃ ፕሮጀክቶችን የመገንባት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስራዎችን መሰራታቸውንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት አስረድተዋል ::

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.