3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛመደበኛ ጉባዔ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለምክር ቤቱ አባላት በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ እንደገለፁት ምክር ቤቱ በመደበኛነት እያደረገ ያለዉ ቁጥጥር እና ድጋፍ በበከተማችን ለተመዘገቡ ተጨባጭ ዉጤቶች ማሳያ ነዉ ብለዋል፡፡
የምክር ቤቱ የህዝብ ተወካዮች አባላት ከወከላቸዉ ህዝብ ጋር በሚያደርጉት ተከታታይ ዉይይቶች የሚመጡ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አስፈፃሚዉ አካላት በግብዓትነት ወስዶ በፍጥነት እንዲያርም በመቻሉ በህዝቡና በመንግስት መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጠር ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሃገራዊና ከተማ አቀፍ የተለያዩ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የድሉ ባለቤት መሆኑን እና በሰላም ወጥቶ በሰላም በግባት መቻሉ የለዉጣችን ማሳያ የሆነ ሌለኛዉ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ እና የፖለቲካ ስብራትን መጠገን የቻለ ድል መሆኑንም ገልፀዋል፡፤
ለዚህም ሶስት አካላት በዋናነት መመስገን የሚገባቸዉና የማይተካ ሚና አላቸዉ ያሉት አቶ ሞገስ ባልቻ የከተማዋ ነዋሪ ፤የፀጥታ መዋቅሩ እና የፖለቲካ አመራሩ ናቸዉ ብለዋል፡፡
የእነዚህን ድምር ዉጤት ስናይ የከተማችንን ገፅታ በመቀየር የከተማችን ተፈላጊነት እንዲጨምር በማድረግ እና ከተማችን ዓለም አቀፋዊ እዉቅና በማግኘት የትኩረት ማእከል እንድትሆን ማስቻሉ ነዉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ሁለተናዊ የድል ሚስጥሩ የገባነዉን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር መስራት የመቻላችን ዉጤት ስለሆነ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠልና ትልቁ ህልማችን ላይ መድረስ ይገባል በማለት ለምክር ቤት አባላትና ለከተማዋ ነዋሪ ልባዊ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.