ዛሬ ያስመረቅነው ባለ 15 ወለል ዘመናዊ የሲኒማ ማዕከል በአይነቱ ልዩና ለኪነጥበብ እድገት አዲስ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን ሳበስር በደስታ ነው !
መንግስት የኪነጥበብን ወሳኝ ሚና በመረዳትና ልዩ ትኩረት በመስጠት በቢሊዮኖች በጀት መድቦ በአይነታቸው ልዩና ዘመናዊ ለሲኒማ ፣ለቲያትር ራሳቸውን የቻሉ ትልልቅ ማዕከላት ሲገነባ ፤ በኪነጥበብ ዘርፈ የተሰማራችሁ ከያኒያንና የጥበብ ቤተሰቦች ሁሉ፣ ለአገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ መሰረት የሚሆኑ የጥበብ ስራዎችን በማበርከት፣ ታሪክ የማይዘነጋው ዘመን ተሻጋሪ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ በማመን ነው ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.