ወንዝና አካባቢ የበከሉ ተቋማትና ግለሰቦች 1.8...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ወንዝና አካባቢ የበከሉ ተቋማትና ግለሰቦች 1.800,000 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ብር ተቀጡ

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ እና በጉለሌ ክፍለ ከተማ 9 ግለሰቦችና  ተቋማት ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በመበከላቸው በደምብ ቁጥር 180/2017 መሰረት (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ አስታወቀ።

 ባለስልጣኑ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
ሁሴኔ አብዳለ 150,000፣ ዳኞ አሞኔ  150,000፣ዝናሽ አሰፋ 100,000፣ኤ,ቲ,ኤ,ኤ ድርጅት  300,000፣ኦሮሚያ ግብርና ህብረት 300,000፣ገዛኸኝ ባዴ 50,000፣ሙላቱ አስረድ 50,000  በአጠቃላይ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር የቅጣት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በተመሳሳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሁለት ግለሰቦች የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ ወንዝና አካባቢውን በመበከላቸው ጌትዬ ነጋሽ እና እነ እሱባለው ማስረሻ እያንዳንዳቸው  150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በድምሩ 300,000 (ሶትት መቶ ሺ ብር) ተቀጥተዋል።

ባለስልጣኑደ የተለያዩ ቆሻሻ በመልቀቅ ወንዝና አካባቢን የሚበክሉ ግለሰቦችና ተቋማት  ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የሚበክሉ ግለሰቦችና ተቋማትን እንደማይታገስ አስታውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታቸው የሚወጡ ነዋሪዎችን እያመሰገነ መላው የከተማው ነዋሪ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ 9995 ነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.