"በኢትዮጵያ ለጥበብ ልዩ ትኩረት በመስጠት ድንቅ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"በኢትዮጵያ ለጥበብ ልዩ ትኩረት በመስጠት ድንቅ ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡ " የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ

ሚንስተሯ ይህን የተናገሩት በትላንትነው እለት ጥቅምት 4/2018 በመዲናዋ የተገነባው አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን በገለፁበት ወቅት ነዉ፡፡

በመዲናዋ አዲስ አበባ የተገነባው አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ ከፍተኛ የመንግስት ባልስልጣናት በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ 

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በምርቃት ስነ ስረዓቱ ላይ እንደተናገሩት የጥበባት ዘርፍ የሀገር ገጽታን የሚገነቡ፤ የማህበረሰብ ቢያኔን የሚሰጡ፣ ለባህል ልውውጥና ዲፕሎማሲ ዕድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወት ዘርፍ በመሆኑ መንግስት የሃገራችን ጥበብ እንዲያድግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በአዕምሯዊ ልማትና ብልጽግና ላይ ጥበባት ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት መንግስት በልዩ ሁኔታ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ትላልቅ የጥበብ ማዕከላትን አስመርቆ ወደተግባር እንዲገቡ መደረጉን ጠቁመዉ ከተማ አስተዳደሩ ላደረገዉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤና ለአመራራቸዉ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መንግስት በየደረጃዉ ከጥበብ ባለሙያዎች ጋር ዉይይቶችና ምክክሮችን ማድረጉ ገልፀዉ  የኪነጥበብ ሙያተኞች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በህግ ማእቀፍ፤በፖሊሲና በአሰራር  እየተፈተሹ ምላሽ እንዲያገኙ እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ለጥበብ ልዩ ትኩረት በመስጠት ድንቅ ስራ እየተሰራ በመሆኑ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች  ኪነጥበብ ለሀገር ግንባታ እና ለህብረብሄራዊ አንድነት ጉልህ ሚና እንዲያዉሉት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.