ባለስልጣኑ በከተማዋ መኪና በማቆም ሽንት የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ በከተማዋ መኪና በማቆም ሽንት የሚሸኑ ግለሰብ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ከዋናው አየር መንገድ ልዩ ስሙ ወሎ ሰፈር አካባቢ መኪና በማቆም  በኮሪደር ልማት ላይ ሽንት በመሽናት ያመለጠ ግለሰብ  ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል  በፈፀመው የደንብ መተላለፍ መሰረት  2000 ብር መቅጣቱን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ አዲስ አበባን ውብና ፅዱ ለማድረግ የተያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ደንብ ተላላፊዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።  

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች  መረጃ  በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.