ዛሬ የከተማችንን ታማኝ ግብር ከፋዮች በታላቅ ድምቀት ሸልመናል ፤ ተሸላሚ ግብር ከፋዮቻችን እንኳን ደስ አላችሁ !ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ግብር ለሀገር ክብር !
ዉድ ታማኝ ግብር ከፋዮች መዲናችን ከእናንተ በምትሰበስበዉ ገቢ በከተማችን በአስደናቂ ሁኔታ የተገበርናቸዉ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት ፣ የህዝቡን የኑሮ ጫና ያቀለሉ ስራዎች ፣ የተማሪዎች ምገባ፣ ከተማችንን ለቢዝነስ እና ለመኖር የተመቸች ንፁህ ፣ ጤናማ አካባቢ እና በአለም አቀፍ ደረጃም ተመራጭና ተወዳዳሪ እየሆነች ይገኛል ፤ ይህ ለዉጥ በርግጥ ለእናንተም ተጨማሪ አሴት፣ለቢዝነስ ማህበረሰቡ ተጨማሪ የሀብት መፍጠሪያ ምንጭ ነዉ።
በቀጣይ በግብር አሰባሰብ ዙሪያ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ይበልጡን ዲጂታላይዝ በማድረግ ፣ በማዘመን እና ተጠያቂነትን በማስፈን ክፍተቶችን እየሞላን ፣ እፀፆችን እያረምን የሁለንተናዊ ብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማን እየገነባን እንሄዳለን ።
በዛሬዉ የእዉቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር ለእዉቅና የበቃችሁ ግብር ከፋዮቻችን ለታማኝነታችሁ ምስጋናዬ የላቀ ነዉ ፣ በተለይም የወርቅ እና የፕላቲኒየም ደረጃ ግብር ከፋዮች የዘርፉ አምባሳደሮቻችን በመሆናችሁ በከተማችን በየትኛዉም መንግስታዊ አገልግሎት እና ኩነት የቅድሚያ ቅድሚ እንድትስተናገዱ እና VIP ፕሮቶኮል እንዲሰጣችሁ መወሰናችንን ስገልፅ ሌሎችም የእናንተን አርአያነት እንደሚከተሉ በማመን ነዉ ።
ግብር ለሀገር ክብር !
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.