የ1ሺህ 445ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከአቅመ ደካማ ወገኖቻችን ጋር በጋራ በመሆን በከተማችን በሚገኙ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ማዕድ በጋራ ተቋድሰናል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ማህበራዊ እሴቶች ፣ የሀይማኖት እና የቋንቋ ብዝሀነት ፣ ውብ የተፈጥሮ ገፅታዎች እና አስደናቂ ህብረ ቀለማት ያሏት ድንቅ አገር ናት፤ ብዝሀነቶቻችን ደግሞ የሚያሰባሰቡ እንጂ የሚያራርቁ አይደሉም፡፡
በዓሉንም ስናከብር ከአቅመ ደካሞች ጋር በጋር በመሆን የሃይማኖት ልዩነቶች ሳይገድበን አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ ልናከብር ይገባል፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የጤና እንዲሆንልን በድጋሚ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
ኢድ ሙባረክ፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.