ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ 400ኪሎ ሜትሮ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ 400ኪሎ ሜትሮች ርቀት በኦሮምያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ2000 ኪሎሜትር ስኴር በላይ ስፋት ላይ ይገኛል።

ፓርኩ በኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ያለውን ተራራ ጨምሮ አስደናቂ የመልክዓ ምድር ገጽታዎችን፣ የዱር እንስሳትን፣ ደኖችን፣ የሳር ምድሮችን እና የተለያዩ የተክል አይነቶችን በመያዙ “የተለያየ አለም በአንድ ፓርክ” ተብሎ ለመጠራት የበቃ ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ባሌ ዞን ገብተው በመገንባት ላይ ያለውን የዲንሾ ሎጅ እና ከባቢውን እንዲሁም የጌሴ የሳርምድርን ተመልክተዋል።

#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.