ወንዞች እና የወንዝ ዳርቻዎችን የበከሉ ድርጅቶች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ወንዞች እና የወንዝ ዳርቻዎችን የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀጡ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የከተማዋን ወንዞችና የወንዞች ዳርቻዎች የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር መቅጣቱን አስታወቋል ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኢትዮ ሌዘር ፋብሪካ ኬሚካል  ፍሳሽን ወደ ወንዝ በመልቀቅ 800,000 ብር ፣ 8 የመኖሪያ ቤቶች እና 1 ድርጅት ያመነጩትን ቆሻሻ ያስወገዱበት መንገድ የወንዞችን ደህንነት ለመጠበቅ የተቀመጠዉን ደንብ የተላለፈ እና የወንዞችን ደህንነት አደጋ ላይ የጣለና ለብክለት የዳረገ በመሆኑ  በድምሩ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ተቀጥተዋል።
በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ረጲ ኮንዶሚኒየም እና ግራር ሆቴል ፍሳሽ ቆሻሻን ከወንዝ ጋር በማገናኘታቸው በድምሩ 600,000 ብር ፤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ዲ ሊዮፖል ኢንተርናሽናል ሆቴል 300,000 ብር ሲቀጣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አቶ ሙሉጌታ መንጋ  እና  አቶ ናትናኤል ገበያው የተሰኙ ድርጅቶች 300,000 ብር ተቀጥተዋል።

ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም ለህብረተሰቡ የተለያዩ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን እየፈጠረ የመጣ መሆኑ ይታወቃል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.