የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
በሩብ ዓመት ሪፖርቱ ከተካተቱ ቁልፍ ተግባራት ውስጥ አገልግሎትን ቀልጣፋ፣ አስተማማኝ፣ ተደራሽና ፍትሃዊ በማድረግ የተገልጋይን ወጪና ጊዜ ለመቀነስ የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በማስመረቅ በማዕከል እና በቦሌ ቅርንጫፍ ወደ ተግባር ተገብቷል።
በዚህ ማዕከል ውስጥ 13 የማዕከል ተቋማት፣ 3 የፌደራል እና 2 የፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊ ሲሆኑ በማዕከል [107] እና በቦሌ ቅርንጫፍ [96 ] አገልግሎቶች ተለይተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ 157የአገልግሎት ካውንተሮች በማዕከል (101) እና በቦሌ ቅርንጫፍ (56) መዘጋጀታቸው ተጠቅሷል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.