የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሩብ ዓመቱ በባህል እና ኪነ-ጥበብ ካከናወናቸው ተግባር ውስጥ:-
👉ቋሚ፣ተንቀሳቃሽና የማይዳሰሱ ቅርሶችን 400 ለመመዝገብ ታቅዶ በደረጃው ባላው አደረጃጀትና ባለድርሻ በመጠቀም ሙሉ ለሙሉ መፈጸም ተችሏል፡፡
👉 ለ406 ቋሚ፣ተንቀሳቃሽ ቅርሶችን ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ ተችሏል::
👉 3 ሕዝባዊና መንግስታዊ ብሔራዊ የበዓል ቀናትና ኩነቶችን በማክበርና ክዋኔውን በማስተዋወቅ ታቅዶ የቡሄ ፣መስቀል እና የኢሬቻ ሶስቱም በዓላት በሲንፖዚየም እና በኤግዝብሽን ለማክበር ተችሏል፡፡
👉 ለ 316,311 ተገልጋዮች የንባብ አገልግሎት መስጠት ተችሏል::
👉 116 የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ተዘጋጅተዉ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ አቅዱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት ተችሏል፡፡
👉ለ 62 ተቋማት የሙያ ብቃት አገልግሎት መስጠት ተችሏል።
👉 68 አማተር የኪነ-ጥበብ ክበባትን ለማቋቋም ታቅዶ በተለያዩ ክ/ከተሞች 17 ክበባትን ማቋቋም ተችሏል::
👉 በጠቃሚ ባህላዊ እሴቶችና ሀገር በቀል ዕውቀቶች ፋይዳና ልማት ዙሪያ የውይይት መድረኮችንን ለማዘጋጀት ታቅዶ “የተረጅነት አስተሳሰብ” እና 7ተኛውን የኢሬቻ ፎረም “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት’’ በሚል መነሻ ሀሳብ ሁለት ግዜ ውይይት ማከናወን ተችሏል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.