የአዲስ አበባ ከተማ አስትዳደር በሩብ ዓመቱ ምገባን በተመለከተ ካከናወናቸው ተግባር ውስጥ:-
👉 የተማሪዎች የዩኒፎርም ስርጭትን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ ከ1,029,090 በላይ በነፃ ለተማሪዎች ዪኒፎርም ማቅረብ ተችሏል ፡፡
👉 የተማሪ መማሪያ ደብተር ከ8 ሚሊይን በላይ በነፃ ለተማሪዎች ማቅረብ ተችሏል፡፡
👉 የመምህራን ጋዋን ስርጭት 52,603 የመምህራን ጋዋን ለማሰራጨት በእቅድ ተይዞ ሙሉ ለመሉ ተፈጽሟል፡፡
👉 የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት ሽፋንን ወደ 976,702 በማሳደግ ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ አፈፃፀሙም ከባለፈዉ ተመሳሳይ ወቅት ከነበረዉ በ136,117 ተማሪዎች ብልጫ ያሳያል፡፡
👉በተጨማሪም በ26 የምገባ ማዕከላት በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎችን በቀን ከ36,600 በላይ ሰዎችን እየመገበ ይገኛል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.