የአዲስ አበባ ከተማ አስትዳደር በበጀት ዓመቱ በሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ጤናን በተመለከተ ካከናወናቸው ተግባር ውስጥ:-
👉 የጤና ተቋማት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ በሩብ ዓመት አዳዲስ አዲስ ጤና ጣቢያዎች ተመርቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
👉 የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ያገኙ ከ44,786 በላይ እናቶች አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡
👉 ከእናቶችም ሞት ምጣኔ 0.032 እና ከዛ በታች ለማድረግ ታቅዶ 0.025 ማሳካት ተችሏል::
👉 የጨቅላ ሕፃናት ሞት ምጣኔ 0.88% እና ከዛ በታች ለማድረግ ታቅዶ 0.67% በማድረስ ከያተዘው እቅድ በላይ ማከናወን ተችሏል::
👉በኮልፌና በንፋስ ስልክ የሚገነቡ አዲስ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በአራት ነባር ሆስፒታሎች እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ የማስፋፊያ ግንባታዎች በፍጥነትና በጥራት እየተጠናቀቁ እና የህክምና ግብአቶችም እየተሟላላቸው መሆኑ በሪፖርቱ ትመላክቷል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.