"በበዓላቶቻችን አብሮነትን በማጠናከር ኅብረ ብሔራዊነታችንን እናጠናክራለን!"
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 1,445ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ በተስፋ ብርሃን ቁጥር 2 የምገባ ማዕከል ለአቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራት አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የምገባ ማዕከላትን ገንብቶ ለአቅመ ደካማ ወገኖች በቀን አንድ ጊዜ የምግብ አገልግሎት እንደሚሰጥ አውስተው፣ በእነዚህ ማዕከላት በዓላትን ምክንያት በማድረግ ያለምንም የሃይማኖት ልዩነት የማዕድ ማጋራት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በበኩላቸው በዓላት የአብሮነትና የኅብራዊነት መንጸባረቂያ መድረኮች መሆናቸውን አውስተው፣ በበዓላት ወቅት አጋር አካላትን በማስተባበር የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለሚያደርገው ድጋፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደጋፊ በመሆኑ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.