የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የፓርቲ እና የመንግስት የልማት ስራዎች ግምገማ መድረክ በቡድን ውይይት ተጠናክሮ ቀጥሏል!
የግምገማው መድረክ በበጀት ዓመቱ የሩብ ዓመት ስራዎች አፈፃፀም፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ማሳለጥ፣ የከተማውን ሰላም ማጠናከር፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ማሳለጥ፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ፣ በባለፉት ሶስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄዱ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ;ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ኩነቶች አፈፃፀም፣ ወንድማማችነት እና የእህትማማችነት ዕሴትን በማጎልበት ፣ በጋራ ተግባቦት የነበሩ ስኬቶችን በሚያስቀጥል እና ጉለቶችን በማረም ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬቱ አስተዋፅዖ ማድረግ በሚያስችል ደረጃ ውይይት እየተደረገ ሲሆን ፤ የአመራሩን አቅም የሚያጎለብት የግንባታ መድረክ እንደሆነም ተመላክቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.