ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስናካሄድ የነበረዉ የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረካችን ተጠናቅቋል ።
በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ በሩብ ዓመቱ እና በ90 ቀናት ስራዎቻችን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የትኩረት መስኮች የተገኙ በርካታ አበረታች ዉጤቶችን ይበልጡን አጠናክሮ ለማስቀጠል ፣ የታዩ ጉድለቶችን ፣ ብልሹ አሰራሮችን በፍጥነት ለማረም እና ዉጤታማነትን በወጥነት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ።
በበጀት አመቱ ቀሪ ጊዜያት ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባሮቻችን ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል ፣ በዚህም የኑሮ ጫናን ለመቀነስ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት አቅርቦት መሻሻሎችን ማስቀጠል ፣ የከተማዉን ሰላም ዘላቂ ማድረግ ፣ የገቢ አሰባሰባችንን ማሳደግ ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር የታየዉን ተስፋ ሰጪ ለዉጥ ይበልጡን ማስፋት፣ የስራ ዕድል ፈጠራን በማሳደግ የህዝባችንን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ይበልጡን አጠናክረን የምናስቀጥል ይሆናል ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.