"ቀን ብቻ የምትሰራ ከተማ ሳትሆን አዲሰ አበባ በምሸትም የምትሰራ ከተማም የማድረግ ሥራ ለውጥ እያስመዘገበ ነው"ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከጥቅምት 8-9/2018 ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማ እና ውይይት ተጠናቋል።
በዝግጀት ይባክን የነበረ ጊዜን ወደ ተግባር በመቀየር፣ በሩብ ዓመቱ የህዝብ ጥያቄን ሞላሽ መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች መፈፀም መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
ፈጠራ እና ፍጥነት ለተመዘገቡ ስኬቶች መሰረት መሆናቸውን የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የኑሮ ጫናን ማቃላል ፣ የገበያ ቁጥጥር ማድረግ እና አማራጭ ምርት እንዲቀርቡ ተደርጓል።
በተጨማም አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ፥ በአረንጓዴ ልማት ፣ በፅዳትና ጐርፍ መከላከልን ትኩረት ተደርጐ በመሠራቱ ውጤት ተመዝግቧል ።
በእውቀት የታነፀ ትውልድ ለመንንበት በ ትምህርት ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።
ወጣቶች በአእምሮም በአካልም ብቁ እንዲሆኑ ፣ ህፃናት ቦርቀውና ተጫውተው እንዲያድጉ ፣ ታለንታቸዉን አወእጥተው እንዲያሳዩና እንዲያሳድጉ የሚያስችሉ መጫወቻ ስፍራ እና መሰልጠኛ የስፓርት ማዘውተሪያዎች ተገንብተዋል።
የሴቶችን ማህበራዊ ተጋላጭነት ለመቅረፍም በነገዋ የክህሎትና ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ሴቶችን በማስልጠን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል። አሁንም ተጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።
አዲሰ አበባ ቀን ብቻ የምትሰራ ከተማ ሳትሆን፣ በምሸትም የምትሰራ ከተማ የማድረግ ሥራ ለውጥ እያስመዘገበ ነው ።
አገልግሎት አስጣጥን ለማሻሻል ውጤታማ የሆነ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም፣ አሁንም አመራሩ ይበልጡን ትኩረት ሰጥቶ ኃላፊነት ወስዶ ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል።
በተቋም መካከል የአፈፃፀም ልዩነቶች በዋናነት የሚፈጠሩት ከአመራር ብቃት እና ስንፍና ጋር የሚያያዙ በመሆኑ ለተሻለ ለውጥ ያለ እረፋት 24/7 የሚሰራ ፥ አገልጋይ አመራር መሆን እንደሚገባም አሳስበዋል ።
በከተማችን የመሰረተ ልማት ጥያቄ አዳጊ ትክክለኛ መሆኑን የገለፁት ከንቲባ አዳናች አቤቤ በቀጣይም አጠቃላይ ሥራዎቻችን በቅደም ተከተል በእቅድ የሚመሩ ይሆናል ብለዋል ።
በቀጣይም የከተማችንን ሠላም ከህዝባችን ጋር ማረጋገጥ ፥ የቤት አቅርበትን ማሳደግ፥ አገልግሎትን ለማሻሻል መሶብ የእንድ ማዕከል ዲጅታል አግልግሎት መገንባትና በሰዉ ሃይልና በቴክኖሎጂ ብቁ ማድረግ ፥ የኑሮ ውድነትን ማቃላል የሚያስችሉ ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ፥ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ማሳደግ ፥ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ማጠናከር፥ የትራንስፖርት ሰርዓቱን ማዘመን ፣ በኮሪደር የለሙ መሰረተ ልማቶች ህዝብ እንዲጠቀምባቸው በአግባቡ ማስተዳደር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አመላክተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.