የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች ወደሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈቃድ ሰጠ።

ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ አድርገው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሊዝ ባለይዞታዎች በተሻሻለው የከተማ መሬት ሊዝ ደንብ 162/2016 አንቀጽ 54 ንዑስ አንቀጽ 1-11 መሠረት የአገልግሎት ለውጥ አድርገው በሕጋዊ መንገድ   
እንዲንቀሳቀሱ ቢሮዉ ፍቃድ ሰጥቷቸዋል። 

በዚህም በእስካሁኑ ተፈቅዶላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ ባለይዞታዎች 2,969 ሲሆኑ 2,581 (86%) የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ወይም የንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል። 

በበጀት ዓመቱ ከዚህ የአገልግሎት ለውጥ 2.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉና ለውጥ የተፈቀደላቸው የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ-ክፍያ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸውም ቢሮው አሳስቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ና አስተዳደር ቢሮ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.