የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር 1 ሺህ 445ኛውን የኢድ-አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷል።
አብሮነታችን እና መተሳሰባችን ለብልፅግናችን መሰረት ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሁላችንም በየእምነታችን ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየዘራን መነጣጠልን አውግዘን አንድነትን እያበረታታን የምንፈልጋትን ኢትዮጲያን እውን ማድረግ አለብን ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) በበኩላቸው ያለው ለሌለው ማካፈል የእኛ ኢትዮጲያዊያን መለያ እሴት ነው ብለው ይህንን እሴታችንን አጠናክረን በማስቀጠል አንድነታችንን ብሎም ልማታችን ማፋጠን ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።
የለውጡ ጉዞ በስኬት የሚቋጨው ይህንን አንድነታችንን መደጋገፋችንንና ፍቅራችንን ማጠናከር ስንችል ነው ያሉት ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በፆም ወቅት የነበረን መተሳሰብ በሌሎች ስራዎችም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.