በመዲናችን "በጎ ፈቃደኝነት ለሀገር መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የበጎ ፈቃደኞች የእዉቅና ሽልማት መርሀ ግብር በዛሬዉ ዕለት ተካሔዷል።
በዚህ የእዉቅና መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ እንደተናገሩት ለወገን፣ለሀገር በጎ ማድረግ የሚያጎድል አንዳችም ምክንያት ያለመኖሩን ጠቅሰዉ ለወገንና ለሀገር በአንድነት በጎ በማድረግ መኖርና በአንድነት አንድ ሆኖ መሞት እጅግ ተፈላጊ እና ታሪካዊ ሀላፊነት ነዉ ብለዋል።
በዚህም አርአያነት ያለዉ ተግባር የፈፀማችሁ በጎ-ፈቃደኞች እኛ ባንናገርም ስራችሁ በራሱ ህያዉ ሆኖ የሚናገር ተጨባጭ እዉነታ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
እኛ ኢ ትዮጽያዉያን ዘር ፣ቀለም እና ቋንቋ ሳይለየን ብዝሀነትን ጠብቀን ለጋራ ልማትና እድገት በጋራ በመቆማችን ልንኮራበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ ሲሉም ተናግረዋል።
አክለዉም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ዉብ እና ምቹ ለማድረግ ሌት ከቀን ሐሩርና ዉርጭ ሳይበግራችሁ ብዙ ዋጋ ለከፈላችሁ ክብርት አዳነች አቤቤን እንዲሁም በየደረጃዉ ያላችሁ የከተማ እስተዳደሩ አመራሮች እውቅና ሊሠጣችሁና ልትመሠገኑ ይገባል በማለት በፌደራል መንግስቱና በራሳቸዉ ስም አድናቆታቸዉን እና ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
በመጨረሻም ተሸላሚዎችን በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት የተከበሩ አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ምንግዜም ለበጎ ስራ ስንተባበር ፈጣሪ ከጎናችን ነዉና የበለጠ በጋራ ተግተን ስንሰራ የማንሰራራት ዘመናችንን እዉን ይሆናል በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.