ዛሬ በከተማችን በ 2ኛዉ ምዕራፍ ተጀምረዉ በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ አካላትን አመስግነናል:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ በከተማችን በ 2ኛዉ ምዕራፍ ተጀምረዉ በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ለ አራቱ ማለትም (1) ከመስቀል አደባባይ መገናኛ - ሳዉዝ ጌት፣ (2) ከአንበሳ ጋራዥ -ጎሮ ፣ (3) ከአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል ፣ ጎሮ ፣ቦሌ ቪ አይ ፒ ተርሚናል እንዲሁም ከሳር ቤት -ጀርመን አደባባይ ፣ጋርመንት ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ አካላትን አመስግነናል ።
በዚህም በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት ሌት እና ቀን ሲሰሩ ለነበሩ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪዎች ፣ማህበራት ፣በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎችም ለነበራቸዉ ከፍተኛ አስተዋፆ እና ትዉልድ ተሻጋሪ ስራ አመስግነናል ።
በተለይም መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ለሚነዙ ሀሰተኛ አሉባልታዎች ጆሮ ሳይሰጥ የልማት ተነሺ የሆኑትም ያልሆኑትም ለጋራ ልማት በመተባበር ፣ ቡና እያፈላ ፣ ዉሃ እያቀረበ ለልማት ስራዉ ዉጤታማነት ላሳየዉ ከፍተኛ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለዉ ።
በ 1ኛ እና በ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተጠናቀቁ መሰረተ ልማቶች መካከል 342 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣ 185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ ፣241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣ ዘመናዊ የመንገድ መብራቶች ፣ በርካታ የህዝብ መገልገያ እና መዝናኛ ቦታዎች ፣ በርካታ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ፣ 101 የህፃናት መጫወቻዎች ፣ 155 የስፓርት ማዘዉተሪያዎች ፣ 153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች እንዲሁም 210 የሕዝብ መፀዳጃዎች ተገንብተዉ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ፣
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዞቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.