ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የብሪክስ ዓለም አቀፍ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የብሪክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት አባል አገራት ዋና ከተማ ምክር ቤቶች ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ በሩሲያዋ ዋና ከተማ ሞስኮ ተፈራርመናል።

ሩሲያ ባዘጋጀችው የ2025 ዓለም አቀፍ የብሪክስ ፎረም፥  በሞስኮ ከተማ ምክር ቤት አስተባባሪነት እየተካሔደ ባለው የአባል ሀገራት ዋና ከተማ ምክር ቤቶች መድረክ የተፈራረምነው የግብ ስምምነት በተባበሩት መንግስታት የ2030 የልማት አጀንዳ ማዕቀፍ በከተሞች ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ፣ ትብብርን ለማጠናከር፣ ልምዶችን ለመለዋወጥና የዓለማችንን ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ምክር ቤቶች የሚኖራቸውን ሚና ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ ለመፍጠር ያለመ ነው።

ስምምነቱን የቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ምክር ቤት ከአንድ ዓመት በፊት የፈረመች ሲሆን፥ የቤላሩስ፣ የኩባ፣ የቴህራን፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኡጋንዳ እና የሩሲያ ርዕሰ መዲና ምክር ቤቶች ዛሬ በመፈረም የፓርላማ ጥምረቱን በይፋ ተቀላቅለዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ የጋራ ጥምረት ለከተማችን የአዲስ ምዕራፍ ምክር ቤት ታላቁ የእመርታ ማሳያ ሲሆን አገራችን በብሪክስ አባልነት የተቀዳጀችውን ዲፕሎማሲያዊ ድል በማስቀጠል ከአባልነታችን የምናገኘውን ትሩፋት የሚያባዛ ነው።

ምክር ቤታችን ለዚህ ስኬት እንዲበቃ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ እና በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላደረጋችሁት ድጋፍ ከልብ አመሰግናለሁ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.