በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በምክር ቤት ዓባላት የተነሱ ጥያቄዎች፡

እየተካሄደ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች፡-

1.በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመፍታት ምን ታስቧል? በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች አካባቢ 

2. የፕሪቶሪያውን ስምምነት ወደ ጎን በመተው የኢትዮጵያን ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነት ለማስገባት እየተስራ ያለውን ሂደት አደብ ለማስገዛት ምን እየተሰራ ነው፤ የአሁናዊ የትግራይ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታስ እንዴት ይታያል?

3. የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ውጤታማ እንዲሆን ምን እየተሰራ ነው፤ በዚህ አልካተትም የሚሉ አካላትን በተመለከተስ ምን ታስቧል?

4. የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሂደት እና የመጪው ጊዜ ተስፋ ላይ፤በተለይም ሀገራችን የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጠቀም እየሰራች ያለችውን አስደናቂ ስራ ለህዝቡ ቢብራራ?

5. በቀጣይ የሚገነቡ የቤት ግንባታ ሂደቶችን በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ?

6.መልካም አስተዳደርን በማስፈን በኩል በህዝቡ ዘንድ እየተነሱ ያሉ ችግሮች ይሰማሉ፡፡ ለወደፊቱ መልካም አስተዳደርን የበለጠ ለማስፈን ምን ታስቧል?

7. የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል በተደረገው የመንግስት ሰራተኞችን የደመወዝ ጭማሪ መነሻ በማድረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪና የቤት ኪራይ እየተጨመረ ነውና ይህን ህገወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ ምን እርምጃ እየተወሰደ ነው?

8. ዘንድሮ የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለመደው ሁኔታ ነው የሚካሄደው ወይስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚሰጡ ምክር ሀሳቦችን አካቶ ነው ይህ ከሆነ ጊዜ አያጥርም ወይ ቢብራራ?

9. የዘንድሮው ምርጫ ሰላማዊ እና ፍትሀዊ እንዲሁም እክል እንዳያጋጥመው ምን እየተሰራ ነው?

10. የትምህርት ጥራት የበለጠ እንዲሻሻል ምን እየተሰራ ነው? የመምህራን ብቃትም እንዲሁ?

11. የባህር በር ጥያቄያችንን በሰላምና በሰጥቶ መቀበል ዘዴ ለማምጣት ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ይታያል?

12. የሻቢያን ትንኮሳ አለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲረዳ ምን እየተሰራ ነው?

13. በአባይ ወንዝ ግድብ ምክንያት ከቦታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ምን ታስቧል?

14. በቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ የተጀመረው የወርቅና ሌሎም ማዕድናት ፕሮጀክቶችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ምን ታስቧል?

15. በቤኒሻንጉል ክልል ከማሼ ዞን ተፈቅዶ የነበረው የመንገድ ፕሮጀክት እስካሁን አልተጀመረም ምክንያቱ ቢብራራ?

16. በቀጣይ በአባይ ወንዝ ላይ ለምንገነባው ተጨማሪ ግንባታ ቢታሰብበት?

17. በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በተካሄዱት ጦርነቶች የደረሱ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን ቢጠቅሱልን?

18. የፖለቲካና የህሌና እስረኞች እልባት ቢሰጠው?

19. በህግ ማስከበር ስም ለሚፈፀሙ የዘፈቀደ እስር ለቀጣዩ መርጫ አሉታዊ ሁኔታ እንዳያስከትል ምን ታስቧል?

20. የኑሮ ውድነትና መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን ለማረጋጋት ምን ታስቧል?

21. ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በዘላቂነት በሰላም ለመፍታት ምን ታስቧል?

22. ነፍጥ ካነሱ አካላት ጋር ያለውን አለመግባባት መሰላም ለመፍታት መንግስት ምን አስቧል?

23. የአሲዳማነት አፈርን ለማሻሻል ምን ታስቧል?

24. የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተሰራው ስራ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ቢብራራ?

25. የመድሃኒት አቅርቦትን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት መንግስት ምን አቅዷል?

26.ከፕሮጀክቶች አፈፃፀም አኳያ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የተያዘ እቅድ አለ ወይ ?

27. የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የራሳቸውን ገቢ ለማመንጨት እንዲችሉ ምን እየተሰራ ነው?


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.