#የጠሚሩምላሾች #PMOEthiopia
ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ ቅንጅትን በተግባር ያሳየ ነው።
የእዳ ሽግሽግን በተመለከተ
ኢትዮጵያ አሁን ላይ እዳዋን ለመክፈል ምንም ችግር የለባትም። በሪፎርሙ አመካኝነት ከ4 አስከ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የእዳ ሽግሽግ ተደርጓል። ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎም መንግስት አንድም ዶላር የንግድ ብድር አልወሰደም። ይህም እዳን ለመቆጣጠር ያለንን ጽኑ አቋም ያሳያል።
ግብርናን በተመለከተ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም በሁሉም መመዘኛዎች ከፍተኛ ለውጥ በፍጥነት ማስመዝገብ ችሏል። ለአብነትም ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።
በምርት ደረጃም ሩዝን ወስደን ብናይ ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።
ገቢን በተመለከተ
ያለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ ገቢ ያገኘችበት ነው። ለአብነትም ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።
የዋጋ ንረትን በተመለከተ
መንግስት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት 440 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል። ከዚህም ውስጥ 160 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ለደሞዝ ጭማሪ ድጎማ የተደረገ ነው። ለነዳጅም 140 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል። በዚህም የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት ወደ 11 ነጥብ 7 ወርዷል። ይህም ከሪፎርሙ ዘመን ጀምሮ ትንሹ የዋጋ ንረት ሆኖ ተመዝግቧል። በቀጣይም ይህን አሃዝ ወደ አንድ አሃዝ ለማውረድ ይሰራል።
"ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት ያላምንም ጥርጥር ባለሁለት አሃዝ እድገት ታስመዘግባለች።" - ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.