ዛሬ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ500 በላይ ውጤት ካስመዘገቡ 1321 ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ 336 ተማሪዎች እውቅና ሰጥተን አበረታተናል።
በ2016 የትምህት ዘመን የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ ያለፋት 21.3 በመቶ ሲሆኑ በ2017 ወደ 31 በመቶ አድጓል፤ እንዲሁም እንደ ሀገር 100 ፐርሰንት ካሳለፉ 50 ትምህርት ቤቶች መካከል 17ቱ በከተማ አስተዳደራችን ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው።
በተጨማሪም ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች 100 ፐርሰንት ማሳለፍ መቻላቸው የስራችን ውጤታማነት ማሳያ ነው።
በተለይም ዛሬ የማበረታቻ ሽልማት ከሰጠናቸው መካከል አይነ ስውራን እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎቻችን ለገጠማቸው የአካል ጉዳት ፈተና እጅ ሳይሰጡ ላስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት ትልቅ ክብር አለኝ ።
የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ውድ ተማሪዎቻችን በዩኒቨርሲቲዎቹ የሚኖራችሁ ቆይታ የበለጠ እውቀት የምትቀስሙበት፣ ለአገር ለወገን የሚጠቅም ክህሎት ይዛችሁ የምትወጡበት እንዲሆን እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.