"ለዛሬዉ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን ለቀሪዉ ትዉልድ የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ለዛሬዉ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን ለቀሪዉ ትዉልድ የሚተላለፍ ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አካታች የልማት ስራ መርቀን እንካችሁ ብለናልና በተገቢዉ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከንቲባዋ ሳር ቤት - ጀርመን አደባባይ - ጋርመንት ፉሪ የኮሪደር ልማትን በመረቁበት ወቅት እንደተናገሩት ፡፡

ይህ ኮሪደር ልማት በአዲሳ አበባ እስከዛሬ ከተጀመሩት የኮሪደር ስራዎች 11ኛዉ፤በሁለተኛዉ ዙር ከጀመርናቸዉ ዉስጥ 6ኛዉ የሆነና በርካታ የከተማ መልሶ ማልማት ስራዎችን በፍትሃዊነት በዉስጡ ያካተተ ነዉ ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

ከካዛንቺስ ኮሪደር ቀጥሎ ረጅሙና ሰፊዉ የኮሪደር ልማት ስራ ሲሆን 16 .5 ኪሎ ሜትር ርዝመት  ያለዉና 589 ሄክታር የሚሸፍን ነዉ  ።

33 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን በስፋትም ከ5 እስከ 8 ሜትር የእግረኛ እና 13.5 ኪሎ ሜትር የሚሆን የሳይክል መንገድ ያለዉ እና  ማህበረሰቡ  ቋሚ እና ዘላቂ የስራ እድል እንዲያገኝ  ወደ 1100 ሱቆች ተገንብተዉ በጉልት ሲነግዱ የነበሩ ወገኖቻችን በእነዚህ የፀዱ ሱቆች እንዲነግዱ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ወጣቶች ለስፖርት ያላቸዉ ፍቅር የተለየ መሆኑን የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ 20 የስፖርት ሜዳዎች ተገንብተዉ የህብረተሰቡን ፍላጎትና ጥያቁ መመለስ የተቻለበት እና ተጨማሪ 20 የህፃናት መጫወቻ ሜዳዎች ተዘጋጅተዉ ለአገልግሎት ከፍት መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

40  የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ያካተተዉ ይህ የኮሪደር ልማት 5.2 ኪሎ ሜትር የሚሆን የወንዝ ዳርቻ ልማትም ተሰርቶ ህብረተሰቡን ከጤና ጠንቅ ነፃ እዲሆኑ የሚያስችል ነዉ ተብሏል፡፡

ከተማን ከተማ የሚያሰኙ የከተማ ስታንዳርድ የሚጠይቃቸዉን ሁሉ የተካተተበትን፤በርካታ ጎስቋላ ገፅታዎች አበባ መስለዉ እና ፍክት ብለዉ የተሰሩበትን፤ለዛሬዉ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን ለቀሪዉ ትዉልድ የሚተላለፍ ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አካታች የልማት ስራ መርቀን እንካችሁ ብለናልና በተገቢዉ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም የመስራት ባህላችንን የበለጠ አጠናክረን በቀጣይ ህዝባችን የሚጠይቃቸዉን ሌሎች ስራዎችን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ እንደምንሰራ እርግጠኞች ነን በማለት ከልማቱ ጎን አብረዉ ለነበሩ አካላት ምስጋናቸዉን አቅረበዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.