በኮሪደር ልማት እና በመልሶ ማልማት የተነሱ ነዋ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በኮሪደር ልማት እና በመልሶ ማልማት የተነሱ ነዋሪዎችን አዲስ በገቡባቸው የመኖሪያ ቤቶች የበዓል አስቤዛ ይዘን በመገኘት ቤት ለእንቦሳ ብለን ጎብኝተናቸዋል።

ነዋሪዎቹ በተተካላቸው መኖሪያ ቤቶች ማህበራዊ ትስስራቸውን ጠብቀው ብዙም ሳይበታተኑ ተመሳሳይ የመኖሪያ አካባቢ እና ብሎክ ላይ በመግባታቸው እንዲሁም የተሻለ የኑሮ ዘይቤ፣ የተሟላ የመኖሪያ ቤት፣ ንጹህ ውሃ፣ መጸዳጃ ቤት፣ የማብሰያ ክፍል፣ ትምህርት ቤት፣ የጤና ጣቢያ እንዲሁም ለልጆች የመጫወቻ የሚሆኑ ቦታዎችን በማግኘታቸው መደሰታቸውን ነግረውናል።

ሌሎች መሟላት ያለባቸውን እና የጎደሉ ነገሮችንም፣ ለአብነት ያህል የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና የመብራት መቆራረጥ በአስቸኳይ እንድናስተካክል የጠየቁን ሲሆን ለነዋሪዎቹ የተሻለ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የጀመርነውን ስራ በፍጥነት እናጠናቅቃለን።

አዲስ አበባችን ማንንም የማትገፋ የሁላችን መዲና ናት። ቃላችንን በተግባር መንዝረን አዲስ አበባን ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ፣ ውብና ምቹ ፣ ማኅበራዊ ፍትህ የነገሰባት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.