የአራዳ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት አዲስ ለተደራጁ 305 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ የሱቅ ቁልፍ በዛሬዉ እለት አስረክቧል፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት አዲስ ለተደራጁ 305 ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ የሱቅ ቁልፍ ለ610 ወጣቶች በዛሬዉ እለት የተለያዩ የመንግስት አካላትና የክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች በተገኙበት በይፋ ርክክቡን ፈፅሟል፡፡
በርክክቡም ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ህይወት ለመለወጥ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን ገልፀዉ በዛሬዉ እለት የመስሪያ ቦታ የተረከባችሁ ወጣቶች ፈጥናችሁ ወደስራ በመግባት የራሳችሁንና የህዝባችሁን ህይወት መለወጥ ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መቅደስ ተስፋዬ በበኩላቸዉ በኮሪደር ልማት ስራ በርካታ የክፍለ ከተማዉ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልፀዉ የስራ እድል የተፈጠረላችሁ 610 ወጣቶች በከተማችን ለምናካሄደዉ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የራሳችሁን አሻራ እንድታኖሩ አብረን እንሰራልን ብለዋል፡:
የስራ እደል የተፈጠረላቸዉ ወጣቶች በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ስራ ለመግባትና መንግስትንና ህዝባቸዉን ለማገልገል ቃል መገባታቸዉን በቁልፍ ርክክቡ ወቅት ገልፀዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.