ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን በተካሄደው Compact with Africa (CwA) መርሃ ግብር ላይ ተካፍለዋል።
መርሃ ግብሩ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የወደፊት ትልሙን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በንግግራቸው የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት ሥራዎችን፣ እንደ ገበያን ክፍት የማድረግ ተግባራት፣ የቁጥጥር ማህቀፎች የማጠናከር ሥራዎች፣ የካፒታል ገበያዎችን የማበርታት እንቅስቃሴዎች ያሉ የኢትዮጵያን ወሳኝ የኢኮኖሚ ሪፎርም ሥራዎችን አንስተው የረጅም ጊዜ የግል ኢንቨስትመንትን በመሳብ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ እንዳስቻሉ አውስተዋል። መርሃግብሩ Compact with Africa 2.0 የአፍሪካን ብሎም የሰፊውን አለም የጋራ ብልጽግና በማሳደግ ረገድ ከፍ ያለ ርዕይ ሊይዝ እንደሚገባ ጥሪ በማስተላለፍ ተጠናቅቋል።
#PMOEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.