ዛሬ ክቡር የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብለን፣ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ አስጎብኝተናቸዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ክቡር የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በምድረ ቀደሞቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ ከተማችን አዲስ አበባ የሚኖርዎት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.