የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የሲንጋፖር ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግን በክብር ተቀብያለው።

ውይይታችን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለንን ግንኙነት ለጋራ ነጋችን ወሳኝ በሆኑ መስኮች በጋራ ለመሥራት በምናደርገው ጥረት ውስጥ አንድ ጠቃሚ ርምጃ ነው። በተለይም በክሂሎት ልማት እና የካርበን ብድር ትብብር ላይ ያደረግናቸው የመግባቢያ ስምምነቶች ጽኑ እና ለነገው ገበያ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞችን ለማፍራት ብሎም በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ዘላቂ፣ ዝቅተኛ ካርበን የሚያወጣ እድገት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው።

ከሲንጋፖር ጋር ይኽን የወዳጅነት እና የትብብር ጉዞ በጋራ በመቀጠላችንም ክብር ይሰማናል። በላቀ ተግባራዊ ትብብር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስን በማልማት፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በገንዘብ ልውውጥ ቴክኖሎጂ፣ ሳይበር ደኅንነት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያለንን ትብብር ለመጠቀም እጅግ ሰፊ አቅም አለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.