ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ አካባቢ የተገነባውን የጉለሌ የተቀናጀ የልማት ስራዎችን በዛሬ እለት በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል::
ፕሮጀክቶቹ በዋነኛነት በአካባቢው እንጨት ከጫካ በመልቀም ለሚተዳደሩ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የሚፈጥሩ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጀምረው የተጠናቀቁ የልማት ስራዎች ናቸው::
የጉለሌ የተቀናጀ ልማት በውስጡ:-
1. ጉለሌ የመኖሪያ መንደር
- የከተማችንን የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ለመጨመር በከተማ አስተዳደሩ ወጪ የተገነቡ ናቸው::
- ባለ 5 ወለል አምስት ህንፃዎች
- 200 አባወራዎችን የሚይዙ
- ሁሉም ቤቶች ዘመናዊ ሆነው የተሰሩ ሲሆን የመኖሪያ መንደሩ ውብ ምድረ ጊቢ አረንጏዴ ስፍራዎች ያካተተ ነው
- በአጠቃላይ 14 ሺሕ 625 ካሬ ላይ ያረፈ ነው
2. ጉለሌ እንጀራ ማዕከል
-ለከተማችን ሁለተኛው የእንጀራ ፋብሪካ ነው
- በዋነኛነት በአካባቢው እንጨት በመልቀም ለሚተዳደሩ 551 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ ነው
- የእንጀራ ማዕከሉ በውስጡ ሁለት የእንጀራ መጋገሪያ ህንጻዎች ፣ የህጻናት ማቆያ ፣ የእህል ማከማቻ ፣ ወፍጮ እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ያካተተ ነው
- 450 ዘመናዊ የእንጀራ መጋገሪያ ምጣድ ተገጥሞለታል
- ዘመናዊ የሊጥ ማቡኪያ ማሽን
- ዘመናዊ የአብሲት መጣያ ማሽን
- ሁለት ወፍጮዎች
- 551 እናቶች በሁለት ፈረቃ ተከፍለው ይሰሩበታል
- በእንጀራ ማዕከሉ ውስጥ የስራ እድል የተፈጠረላቸው እናቶች ከዚህ በፊት በአካባቢው እንጨት በመልቀም ሲተዳደሩ የነበሩ፣ ምንም ገቢ የሌላቸው እና የኑሮ ጫና የበረታባቸው እናቶችን ናቸው
- በአጠቃላይ በ10ሺሕ ካ/ሜ ላይ ያረፈ ማዕከል ነው
3. ጉለሌ የወተት ማዕከል
- የወተት ላሞች ሼድ
- የመኖ ማከማቻ መጋዘን
- የጥጃ ቤት ፣ የሰራተኞች ማረፊያ እና መጸዳጃን ያካተተ ነው
- በአሁኑ ወቅት ከበጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶች በተገኘ ድጋፍ 48 የወተት ላሞች ተገዝተው ስራ ጀምሯል
- በወተት ላሞች እርባታ ላይ ሥራ አጥ የሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች በ4 ማሕበራት ተደራጅተው ስራ ጀምረዋል
4. መንገድ
የአካባቢውን የመንገድ ትስስር የሚያሳድግ ዘመናዊ 2.5 ኪ/ሜ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ተከናውኗል
5. የምገባ ማዕከል
የዚሁ የጉለሌ የተቀናጀ ልማት ስራ አካል የሆነው ቀጨኔ የተስፋ ብርሃን የቶኩማ ስታር ቢዝነስ ቅርንጫፍ የምገባ ማዕከል ግንባታው ቀድሞ እንዲጠናቀቅ በመደረጉ ቀድሞ ለአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት የጀመረ ነው::
በአጠቃላይ በዚህ የተቀናጀ የልማት ስራዎች ለ1533ነዋሪዎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.