የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎችን የቤት ባ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል!

አስተዳደሩ የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በመንግስት ፣ በበጎ ፈቃድ (ኢኒሼቲቭ) እና በግል ገንቢዎች (አልሚዎች) ትብብር በርካታ ቤቶችን በመገንባት በፍትሐዊነት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

በዚህም በተለያዩ አማራጮች ቤቶችን በመገንባት፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን በማሻሻል አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡

አስተዳደሩ ከግል ባለሀብቶች ጋር በቅንጅት በመስራት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማሟላትና ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

እስካሁን ድረስ በተለያዩ ፕሮግራሞች የተከናወነው ዝርዝር የሚከተለው ነው፦

በኮንዶሚኒየም ፕሮግራም:- 139,008

ለአቅመ ደካሞች እና ለአገር ባለዉለታዎች (በመንግስት እና በበጎ ፈቃደኞች ትብብር የተገነቡ):- 40,576

በከተማ አስተዳደር ለኪራይ የተገነቡ:- 24,819

በሪል እስቴት፣ በማህበር እና በግል ገንቢዎች የተገነቡ:- 175,605

በድምሩ ከ380,000 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል፡፡

በቀጣይም የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.