የረዳን ፈጣሪ ይመስገን! በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ አካባቢ ለሚኖሩ ወገኖቻችን በገባነው ቃል መሰረት “ቃል በተግባር” ብለን የተቀናጁ ፕሮጀክቶች ጨርሰን አስረክበናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የዛሬ ዓመት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እንጨት በመልቀም ሲተዳደሩ ለነበሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የጉለሌ አካባቢ እናቶች እና የስራ እድል ያላገኙ ወጣቶች ጥያቄ መሰረት፦
1. ለከተማችን ሁለተኛ የእንጀራ ፋብሪካ የሆነው የጉለሌ እንጀራ ማዕከልን፣
2. ጉለሌ የመኖሪያ መንደርን ፣
3. ጉለሌ የወተት ምርት ማዕከልን ፣
4. የምገባ ማዕከልን እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ግልጋሎት የሚሰጥ የመንገድ ስራን፣
እነሆ በቃላችን መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለ1533 ነዋሪዎች የስራ ዕድል በመፍጠር ዛሬ አገልግሎት አስጀምረናል።
ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን በመወጣት የጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደር እውን እንዲሆን ድጋፍ ያደረጋችሁትን ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ፣ ኢ/ር መታሰቢያ ታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ፣ ማህደር ገብረመድህን ኃ/የተ/የግ/ኩባኒያ እና ድሪባ ደፈርሻ ጄነራል ኮንስትራክሽን እንዲሁም ፕሮጀክቱን ላስተባበራችሁ አካላት በሙሉ በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.