ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመዲናችን አዲስ አበባ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመዲናችን አዲስ አበባ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል።

የስልጠናው መሪ ሀሳብም "በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ" ሲሆን፣ ለብልፅግና ፓርቲያችን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የተሰጠ የሁለተኛ ዙር ስልጠና ሲሆን፣አመራሩ በሁሉም መስኮች በስልጠናዉ ያገኘዉን ግንዛቤ በተጨባጭ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን እና የተገኙ አበረታች ውጤቶችንም የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

በሁሉም መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ወደ ድል በመቀየር፣ የተሻለችና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ትኩረት እንዲደረግባቸዉ ባስቀመጥናቸዉ የግብርና እና ገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ እንዲሁም የቱሪዝምና ከተማ ልማት ዘርፍ እምርታን ለማስመዝገብ መግባባት ፈጥረናል።

በማያቋርጥ “መፍጠር እና መፍጠን “ መርህ እየሰራን የኢትዮጵያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.