20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን

የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያና የጋራ ድምቀት በሆነችው በመዲናችን አዲስ አበባ ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ሎሚ በዶ፣ የሁሉም ክልሎች ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች  እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በከተማችን የኢትዮጵያዊያንን ህብረ-ብሔራዊ አንድነት በሚያጎላ መልኩ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት፣ ውብና ታሪካዊ ሆኖ በተገነባው አራዳ ፓርክ በአዲስ አበባ ደረጃ አክብረናል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በመዲናችን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ስናከብር፣ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዟችንን መሰረት መገንባትን ይበልጥ የምናረጋግጥበት እና በብዝሃነት  ደምቀን አንድነታችንን  በሚያጠናክር መልኩ  ነው።

ኢትዮጵያችን ታይታ የማትጠገብ፤ ምድረ ቀደምት፤ የብዙ  ባህልና ቅርስ  ሀብቶች እንዲሁም  የጀግንነት ታሪክ ባለቤት በመሆኗ  ከትውልድ ወደ ትውልድ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር እጅ ለእጅ ተያይዘን መትጋታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.