ዛሬ በከተማችን በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አምራች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በከተማችን በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተናል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅተን በዘርፉ የስራ እድል  የፈጠርንላቸው እና በግላቸውም በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ስራ የጀመሩ አምራቾች አሁን ላይ ወደ ኢንዱስትሪ ደረጃ  አድገው  በአጭር ጊዜ ፍሬያማ እየሆኑ መምጣታቸውን በማየታችን ደስ ብሎናል።

በጎበኘናቸው ኢንዱስትሪዎች የተፈጠሩ  የስራ ዕድሎች፣ የምርት ሂደት በተለይም በተኪ ምርት እና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማምረት ረገድ እያከናወኑት ያለው ስራ አበረታች ነው።
የከተማ አስተዳደራችን ለነባሮቹም ሆነ ለአዳዲሶቹ  ኢንዱስትሪዎች ውጤታማነት እያደረገ ያለውን የመስሪያ ቦታ የማቅረብ እና ሁለንተናዊ ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.