በእግር ኳስ ስፖርት የጀመርነው ፕሮጀክት ፍሬ በማፍራት ላይ ነው።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
እንኳን ደስ አለን!
ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ ሲካሄድ በነበረው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ከ17 ዓመት በታች ውድድር፣ ብሔራዊ ቡድባችን የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት ከ 22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ችሏል። ይህ ድል የእግር ኳስ ስፖርት ወዳድ ለሆነው ህዝባችን የዘመናት ቁጭት በቅርቡ መልስ እንደሚያገኝ ያሳየ ነው።
ቀይ ቀበሮዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት ለዘርፉ የሰጠነው ትኩረት ውጤት እያፈራ መሆኑን ማሳያ ነው።
በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም መላው የቡድኑ አባላትን፣ የኢትዮዽያን ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.