በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ተደርገዋል::
በኮሪደር ልማት ምክንያት ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ያለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ ተዘግቶ የነበረው መንገድ በከፊል ክፍት ተደርገዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር
• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር
•ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ እና ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ምልክትና ማመላከቻዎች አክብረው እራሳቸውንና ሌሎችን ከመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ እየጠበቁ መንገዱን መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.