ዛሬ ማለዳ የከተማ አስተዳደራችን በሰጠው ልዩ ት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ የከተማ አስተዳደራችን በሰጠው ልዩ ትኩረት እና ቁርጠኝነት ለ30 ሺህ የከተማችን ወጣቶች እና ሴቶች አዲስ የስራ ዕድል ፈጥረናል ።

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ዉብ አበባ የማድረግ ስራችን የነዋሪዎቿንም ኑሮ እና አኗኗር በመለወጥ ጭምር ነዉ።

ዛሬ ወደ ስራ ያስገባናቸዉ እነዚህ አዲስ ስራ ጀማሪዎች ቀደም ሲል በተለያዩ መድረኮች ስንወያይ የስራ ዕድል ጥያቄ የነበራቸዉ ወጣቶችና ሴቶች ናቸዉ ።

የስራ ዕድል ተጠቃሚዎቹ በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በንግድ፣ በአገልግሎትና በሌሎችም አዋጭ ዘርፎች ላይ በልዩ ሁኔታ በማሰማራት ዛሬ ስራ አስጀምረናል።

ይህ በከተማችን በስፋት እየተተገበረ ያለዉ የአንድ ጀምበር የስራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ በቀጣይነት በልዩ ትኩረት እየተደገፈ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

አስተዳደራችን በቀጣይም በላባቸዉ ፍሬ የሚኖሩ ፣ ሥራ ፈጣሪ ፣ ታታሪ ዜጎችን በሁሉም መስክ መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላል።

በሥራ ዓለም የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ የጀመርነዉን የብልጽግና ጉዞ በሙሉ ቁርጠኝነት እውን ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት በከተማችን ይበልጥ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል።

ዉድ የሥራ ዕድሉ የተፈጠረላችሁ ወጣቶች እና ሴቶች አስተዳደራችን ለእናንተ አስፈላጊዉን ድጋፍ እና ክትትል የሚያደርግላችሁ ሲሆን በተፈጠረዉ እድል በአግባቡ በመጠቀም ጠንክራችሁ በመስራት የራሳችሁን ፣ የከተማችሁን ታሪክ የምትቀይሩ ዉጤታማ ዜጎች መሆን ይጠበቅባቹኋል ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.