በአዲስ አበባ ታላቅ የኢትዮጵያ የምግብ ፌስትቫል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ታላቅ የኢትዮጵያ የምግብ ፌስትቫልና ኤክስፖ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከጎልደን ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት ዛሬ ባደረጉት ስምምነት ይህን ፌስቲቫል በጋራ እንደሚያዘጋጁ ገልጸዋል።

ዝግጅቱን አስመልክተው ሁለቱ ተቋማት የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት በሸራተን አዲስ መግለጫ ሰጥተዋል ።

የምግብ ፌስትቫልና ኤክስፖው በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት ጥር 9 እና 10 በሚሊንየም አዳራሽ እንደሚካሄድም በዛሬው ዕለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደርጓል ።

ይህ ዝግጅት በሆቴልና ሬስቶራንት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች እንዲሁም ግብዓት አቅራቢዎች በቱሪዝም ዘርፍ የሚያበረክቱትን ሚና ለማጠናከር እንዲሁም የሀገራችንን የጋስትሮኖሚ ቱሪዝም ለማስተዋወቅና ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዲሚኖረው የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር ሁንዴ ከበደ ተናግረዋል።

የጎልደን ሆስፕታሊቲ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሼፍ ሄኖክ ዘርይሁን በበኩላቸው ይህ ፌስትቫል የሀገራችን ምግቦችና የአመጋገብ ስርዓትን ለዓለም ለማሳየት ያግዛል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.