የዘንድሮው የአለም ኤድስ ቀን በአለም አቀፍ ደረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዘንድሮው የአለም ኤድስ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ37ኛ ጊዜ "ተግዳሮቶችን በመቋቋም ፣ የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽ ዘላቂነት እናረጋግጥ ! " በሚል መሪቃል ታስቦ ይውላል ።

የአለም ኤድስ ቀን

በሀገራችን የኤችይቪ ስርጭትን ለመከላከል በተሰራው ዘርፈ ብዙ ምላሽ የበሽታውን ስርጭት መቀነስ ተችሏል ።

ህብረተሰቡ እና አጋር አካላት እንዲሁም በዘርፉ የተቋቋሙ ማህበራት በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የነበራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ አሁንም የበሽታው ስርጭት ከቦታ ቦታ የተለያየ ሲሆን በወጣቶች እና አፍላ ወጣቶች ላይ ስርጭቱ የሚታይ በመሆኑ ስርጭቱን ለመግታት ዘርፈ ብዙ ምላሽ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው ።

የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመግታት ሀገራችን ፖሊሲዎችን በመቅረፅ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ተግባራዊ በማድረግ ፣ ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በመሰራቱ የኤች.አይቪ. ስርጭትን ከነበረበት አሁን ላይ  በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል፡፡

ዘንድሮው በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው የአለም ኤድስ ቀን ስናከብር በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህይወታቸውን ያጡትን የምናስብበት በዘርፉ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት ለማጠናከር ቃል የምንገባበት ሲሆን ከተማችን አዲስ አበባ ኤች አይ ቪ የማህበረሰቡ ችግር እንዳይሆን በተሰሩ ስራዎች ስርጭቱን መቀነስ ችላለች  ።

 

ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ሁሉን አቀፍ ፣ ከአድሎና ማግለል ተጽዕኖ ነጻ የሆኑና ቀልጣፋ ማድረግ ዘላቂ የኤችአይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ተግበራን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ መምራት እና መተግበር ትኩረት የሚሰጠዉ ጉዳይ ነው፡፡

ማህበራት፣ የባለድርሻ አካላት፣ እና አጋር ድርጅቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ያስፈልጋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.