በአዲስ አበባ በአገልግሎት አሰጣጥም እንደ ሌሎችም የልማት ስራዎቻችን ሁሉ እምርታ ለማምጣት በትኩረት እየሰራን እንገኛለን !
ከትናት በስቲያ የገቢዎች የደረሰኝ ቁጥጥር በባለሙያዎች ዩኒፎርም ላይ የተገጠመ ድምፅና ምስል የሚወስድ የካሜራ ቴክኖሎጂ መጠቀም መጀመራችን ይታወቃል።
ዛሬም የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ የሚያዘምን አዲስ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ዲጂታል ስርአትን አስጀምረናል።
አዲሱ ሲስተም ባለጉዳዮች የምባይል ስልካቸውን፣ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም በአካል ሳይገኙ ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል፣ የግዴታ ፎርም መሙላትን የሚያስቀር፣ በኢምግሬሽን፣ በጤና፣ በፍርድ ቤት፣ በብሄራዊ መታወቂያ እና በሎሎችም በተቋማት መካከል ቅንጅት እና መናበብን የሚፈጥር ፣ የመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ያለ ባለፋይሉ ባለቤት ይሁንታ ለማንም በእርሱ የቤት ቁጥር መታወቂያ እንዳይሰጥ መቆጣጠር የሚያስችል እና ሌሎችም በርካታ ዝርዝር አገልግሎቶችን አጣምሯል።
ስራ ላይ የዋለው የ Civil Registration and Vital Statistics with ID ሲስተም ከዚህ ቀደም በወረቀት ይሰጡ የነበሩ የተለያዩ እንግልቶችን የሚያስቀር፣ ብልሹ አሰራርን በመከላከልና ግልጽነትን በማምጣት ረገድ የጀመርነውን ሰፊ ስራ ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግ ነው ።
ይህንን ወሳኝ ቴክኖሎጂ በአጭር ጊዜ ላበለፀገው ለኢትዮዽያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወርቁ ጋቸናን እና የኢንስቲቲዩቱን ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች ኤጀንሲ ሀላፊዎችና ሰራተኞችን በራሴና በከተማችን ነዋሪዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.