"ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ብሔራዊ ጥቅ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞቻችን ላይ ወጥ የሆነ መረዳትና አስተሳሰብ ማበልጸግ ይጠበቅብናል " - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ሀገራዊ መግባባት እና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ሚና” በሚል ርእስ ለኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ 

በሥልጠና መርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞቻችን ላይ ወጥ የሆነ መረዳትና አስተሳሰብ መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ 

በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከመሠረታቸዉ በመረዳት የሰላም ግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚና ከፍ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ 

የሥልጠናው ዓላማ የኮሙኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፉን በሥልጠና በማገዝ ወቅታዊ፣ ትክክለኛ፣ የተናበበ እና የተቀናጀ መረጃ ተደራሽነትን ማረጋገጥና ሚዲያን በአጀንዳ ለመምራት ዐቅም ለመፍጠር ነው፡፡ 

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅሞች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂ በመረዳት የሀገረ መንግሥት ግንባታውን በኮሙኒኬሽን ለመደገፍ፣ ለሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ በፍጥነትና በጥራት ለመስጠት እንደሚጠቅማቸዉ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ለሕዝብ እና የንግድ መገናኛ ብዙኃን አመራሮችና ባለሙዎች መሰጠቱ ይታወሳል። 

በዛሬዉ ሥልጠና ደግሞ እስከ 200 የሚደርሱ የኮሙኒኬሽን ዘርፉ አመራችና ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.