“ኢትዮጵያ እየተገነባች ያለችው በራሳቸው በኢትዮ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ኢትዮጵያ እየተገነባች ያለችው በራሳቸው በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን ነው:: ዘ-ስታንዳርድ

“ኢትዮጵያ እየተገነባች ያለችው በራሳቸው በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን ነው፤  አዲስ አበባ የተደራጀችው፣ ከተማዋን ለህዝቧ በዕውኑ እየቀየረች ያለች፣ ቆራጥ እና ታታሪ ሴት ከንቲባ ስላለቻቸው ነው”

አንያንጎ Thee Anyango ኬንያዊቷ የዘ-ስታንዳርድ አምደኛ)

ከሰሞኑ አንድ  አንያያጎ (Thee Anyango) የተባለች  ኬንያዊ ጋዜጠኛ ከተማቸችን አዲስ አበባን ጎብኝታለች፡፡ በቆይታዋም ስለከተማዋ እድገት ከናይሮቢ ከተማ ጋር እያነጻፀረች ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥታለች፡፡ እንደሚከተለው ቀርቧል፡- 

 ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ስትደርሱ መጀመሪያ የሚቀበላችሁ ነገር የቦታው ስፋት፣ ግዝፈት እና ብሩህ መብራት ነው። ከዚያም ስሜትን የሚያድስ ቀዝቃዛ አየር አለ። አዲስ አበባ የሰላም፣ የመረጋጋት እና የፀጥታ መንፈስ የተላበሰች ከተማ ነች።

 መንገዶቹ በጣም ንጹህ እና እጅግ ውብ ናቸው። በዚህች ከተማ ጽዳት የሁሉም ሰው ኃላፊነት ነው። ቆሻሻ መጣል ነውር ነው፤ ያስቀጣልም፡፡ ህዝቡም ህጉን ያከብራል። በመንገዶች ላይ የሚታዩት የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች ሳይቀሩ ጽዳታቸውን የጠበቁ ናቸው።

 በመሀል ከተማ ውስጥ እግረኞች በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ። ትናንሽ ታክሲዎች እና ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በዲሲፕሊን ይሽከረከራሉ። በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የቅንጦት ሳይሆኑ በተግባር የሚታዩ የአኗኗር ዘይቤዎች ሆነዋል። የአውቶቡስ እና የትራፊክ ስርዓቱም እጅግ የተደራጀ ነው።

የሚዲያ ተቋሞቻቸው (Media houses) ልክ እንደ ቶኒ ስታርክ (Tony Stark) ወርክሾፕ ዘመናዊ፣ ሰፊ፣ ንጹህ እና በምርጥ ቴክኖሎጂ የተደራጁ ናቸው።

ከሙዚቃ ጋር የተቀናጁ፣ ብሔራዊ መዝሙርን በድምጽ ማጉያ እያሰሙ የሚደንሱ የውሃ ምንጮች (Dancing water fountains) ለህዝብ ክፍት ሆነው ይታያሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች በብድር ሳይሆን በኢትዮጵያውያን የግብር ገንዘብ የተገነቡ ናቸው።

አዲስ አበባ እንደዚህ የተደራጀችው ከተማዋን ለህዝባቸው ለመቀየር ሌት ተቀን በሚሰሩ ጠንካራ ሴት ከንቲባ አማካኝነት ነው። በአጠቃላይ አዲስ አበባ በኢትዮጵያውያን እጅ ለኢትዮጵያውያን እየተገነባች ያለች መሆኗ በግልጽ ይታያል።

 ኢትዮጵያ እየተገነባች ያለችው በራሳቸው በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን ነው። ይህም ግዙፉን የህዳሴ ግድብ ያካትታል። ይህ ግዙፍ የልማት ስራ የተከናወነው በኢትዮጵያውያን የግብር ገንዘብ እና በህዝብ ተሳትፎ ነው እንጂ፤ እንደተለመደው ከአይ ኤም ኤፍ (IMF) በተበደረ ገንዘብ አይደለም። ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ታሪክ በራሳቸው አቅም እየጻፉ ነው።

ምንጭ፦ ዘ-ስታንዳርድ (ኬንያ)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.