የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በቅንጅት እየ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉጽት 9 ወራት በቅንጅት የተሰሩ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም በጋራ ገምግመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቢሮዉ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማጠናከር የፀጥታ መዋሩን ከማህበረሠቡ ጋር በማቀናጀትና የሠላም ባለቤት እንዲሆን በማስቻል በፈጣን የመረጃ ቅብብሎሽ ዐረ ሰላም ሀይሎች የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን በማጨናገፍና በመቆጣጠር ህገ ወጥ እና አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል እና ህጋዊ እርምጄ በመዉሠድ ደረቅ ወንጀሎችን በመቀነስ በቅንጅት የተሳካ ስራ መስራት ችለናል ብለዋል፡፡

ሀላፊው አከለዉም ዘላቂ ሠላም በከተማችን እንዲሰፍንና ሌብነትና ብልሹ አሠራርን ከመዋጋት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የተደራጀው የሠላም ሠራዊቱ እና የሠላም ባለቤት በመሆን እየሠራ የሚገኘው የከተማችን ነዋሪ ከአመራሩና ከባለሙያዉ ጋር በመቀናጀት መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይም የተቋማቱን አቅም በአሰራር በሰዉ ሃይልና በቴክኖሎጂ በማዘመን በተቀናጀ አግባብ እነዚህን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡:

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸዉ የመሬት ወረራን በማስቆም እና የተወረሩ መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ በማስገባት ህገወጥ ግንባታና የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ዉጤት ያስመዘገብነዉ በቅንጅት ስለሰራንና የአመራር ፑል በመጠቀም ወጥነት ያለዉ ግምገማ በመዋቅራችን ዘርግተን ስለሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

የዉይይቱ ተሳታፊዎችም ተቋማቱ ስኬታማ ያደረጋቸዉ ስራዎች በተቀናጀ አግባብ ቀን ከሌት በመሰራቱ ስራዉ በአግባብ የተመራ በመሆኑ እና ከማእከል እስከ መንደር የሥራዉ ባለቤት በመሆን በቁርጠኝነት በመሳተፋቸዉ መሆኑን ገልፀዉ በቀጣይ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማሳደግ የጋራ አቋም በተያዘባቸዉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.