የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን 1ኛውን የከተማ የቱሪዝም ፎረም ማዘጋጀቱን ገለጸ፡፡
የአዲስአበባ ቱሪዝም ኮሚሽን የከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለማስተዋወቅ፣ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የዘርፉ ተዋናዮች የሚሳተፉበትን አንደኛውን የቱሪዝም ፎረም ከታህሳስ 05-07/2018 ዓ.ም በአራዳ ፓርክ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡
ዝግጅቱን አስመልክቶ ዛሬ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከተማዋ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በማልማትና በማስተዋወቅና ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ አንደኛው ቱሪዝም ፎረም፤ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የቱሪዝም ንግድ አውደርዕይ፣ የከተማዋን የቱሪዝም መደራሻዎችና ልማቶች የሚያሳይ የፎቶ ኤግዝቢሽን፣ ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተማዋን የሚያስተዋውቅበት የዲጅታል ፕላትፎርሞችና ማስታወቂያዎች ይፋ የሚደረጉበት እና የዘርፉ ምሁራን የሚሳተፉበት የፓናል ውይይትን ያካተተ መርሀ-ግብር መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.