የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለንተናዊ ብልፅ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ጉዞ ፅኑ መሰረት እንዲይዝ ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል፤ እየተከናወኑም ነው።

በዚህም የተለያዩ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ሃይል በማደራጀት ቀልጣፋ እና ዘመኑን የዋጀ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ 

ከዚህ ቀደም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይስተዋል የነበረውን የተበታተነ እና ኋላ ቀር  አስራር በዘመነ መልኩ በማቅረብ አገልግሎት ለማግኝት ይባክን የነበረዉን  እንግልት፤ገንዘብ እና ጊዜ በማስቀረት ለተገልጋይ እፎይታን መስጠት ተችሏል፡፡

በከተማ ደረጃ በርካታ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘዉ "የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት (አዲስ የአገልግሎት አድማስ)" የዚሁ አንዱና ዋነኛዉ ማሳያ ሲሆን ማዕከሉ በአደረጃጀት፣ በአሰራር ስርዓት እንዲሁም በሥነ-ምግባር አርአያ የሆኑ ሰራተኞችን እና ጠንካራ የአሰራር ስርዓትን ዘርግቶ ነፃ እና ፍትሃዊ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ነዉ፡፡

ህብረተሰቡ ከዚህ ቀደም ቅሬታ ያነሳባቸው የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለዉ በመሆኑም ማዕከሎችን በሌሎች ክፍለ-ከተሞችም የማስፋፋት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ሁለንተናዊ የከተማ ልማት ለዕድገት መሰረት መሆኑን የተረዳው ከተማ አስተዳደሩ ከሚሰራቸው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን በአገልግሎት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በቴክኖሎጅ አቅም ተጠናክረው ለህብረተሰቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.