በፈረንጆቹ 2027 በኢትዮዽያ የሚካሄደዉን 32ኛ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በፈረንጆቹ 2027 በኢትዮዽያ የሚካሄደዉን 32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል።

አዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ብቻ 150 ያህል ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት በማከናወን ተመራጭ መዲና መሆኗን አረጋግጣለች፣ በዘንድሮዉ አመት ብቻ  እስካሁን 105 የተለያዩ ኮንፍረሶችና አለም አቀፍ ኩነቶች በመዲናችን አዲስ አበባ ተካሂደዋል ።

ለዚህም የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ጠንካራ ትብብር ጉልህ ሚና ነበረው።
ዛሬ ከከተማችን ባለሀብቶች፣ የሆቴል፣ የሪልስቴት፣የቱሪዝም ፣ የንግዱ  ማኅበረሰብ  እና የጠቃላይ የአገልግሎት ሰጪ ዘርፎች  ጋር ጉባኤውን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል፤ ግብረሃይል በማቋቋምም የሥራ ክፍፍል አድርገናል ።

ውድ የከተማችን ባለ ሀብቶችና የንግዱ ማኅበረሰብ፣ ለሰጣችሁን ጠቃሚ ግብዓት፣ ሐሳብና አስተያየት እንዲሁም ለወሰዳችሁት ኃላፊነት፣ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

በቀጣይም ቅድመ ዝግጅቶችን እየገመገምን፣ ከምንጊዜውም የተሻለና ደማቅ ጉባኤ ለማካሄድ በቅንጅት እንሠራለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 
  
 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.